ቃለ መጠይቅ| ኬፋ ሚደቅሳ ቄሮን ደግፎ ለዘማሪ ደረጀ ምላሽ ሰጠ
BELOW IS THE AMHARIC VERSION OF YEROO MEDIA INTERVIEW WITH POPULAR GOSPEL SINGER & PASTOR KEFA MIDEKSA
CLICK HERE for Afan Oromo version
የሮ: ደረጀ በኢትዮ360 ሚዲያ ከርእዮት ጋር ያደረገዉን ቃለ ምልልስ ተከትሎ ያነሳኸዉን ሃሳብ በተመለከተ የኢትዮጲያኖች ምልሽ ምን አይነት ነበር?
ኬፋ: ይሄን ሃሳብ በሁለት መንግድ አየዋለው አንዱ የኢትዮጵያ ህዝቦች ብሄሮችና ብሄረስቦች በሃሳብና በአመለካከት የተለያዩ ናቸዉ እንዲሁም ደግሞ የኔን ሃሳብ እንዳለ ወስደዉ ሚደግፉም አሉ እንዲሁም የተቃወሙም አሉ ይሁን እንጂ ሁሌም የምናድርገዉና የምንናገረዉም ለህዝባችን ድጋፍ መሆን አልበት የሃይማኖት መሪዎችም ማድረግ ያለብን ተስፋ ለቆረጡት ተስፋ መሆን አለብን እንጂ ለእርስ በርስ ጥፋት መሳሪያ መሆን የለብንም፡ ደረጀ በአደባባይ ኢትዮጵያ ፈርሳልች ብሎ ተናግሮአል እዉነት ለመናገር ዶር ደረጀ በጣም ትልቅ ሰዉ ናቸዉ በቀደሞዉ በደርግ ስርአት እንኳን ብዙ ችግር አሳልፈዋል ዋጋም ከፍለዋል ታዲያ በፊት ከነበራዉ አቋም ወርደዉ እንደዚ ሳያችዉ በጣም አዝኛልው እንደ ሃይማኖት አባትም ይሄን ከሱ አንጠብቅም ነበር የአንድ ብሄር ደጋፊ ሆኖ ስለመፈራረስና ስለመብታተንም ማውራት አልነበረበትም።
የሮ: ዶር ደርጀ የኦሮሞ ወጣቶችን በመፈረጁ ተቃርኖ አሰምተሃል ይህን ሲል ጥፋት ያጠፉትን አንዳንዶችን ነው ወይስ ሁሉንም የኦሮሞ ወጣት ያማከለ ነዉ ምን ለማለት ፈልጎ ይመስልሀል
ኬፋ: __ ቄሮ ማለት የኦሮሞ ወጣት ነዉ ነገርግን ደረጀ በኦሮሚያ ዉስጥ ለሚከሰተዉ ጥፋት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂነት መዉሰድ ኣለብት ብሎ መናገሩ ትልቅ ሰህተት ነዉ ቀጥሎም ቄሮ ኢትዮጲያ ዉስጥ ከሚኖሩ ወጣቶች መካከል ፋኖ የአማራ ኤጀቶ የሲዳማ እና ዘርማ የጉራጌ እንደሚባለዉ ከማህበረስቡ ክፈል አንዱ ነዉ እንዲሁም ደግሞ እነዚህ ወጣቶች ለዉጥ ለማምጣት ብዙ ታግለዋል በተለይ ቄሮ ብዙ ዋጋ ከፍሏል ይሄን ስል ደግሞ በስመ ቄሮ የሚንቀሳቀሱና ህዝብን ከህዝብ ጋር ሚያፋጁ የሉም እያለኩም አደለም
የሮ: አንደምናዉቀዉ ደረጀ አንጋፋዉ የክርስትያን ዘማሪ ነዉ የኦሮሚኛም መዝሙሮች አሉት ነገር ግን አሁን በተናገረዉ ነገር ይቅርታን መጠየቅ አለበት ብለህ ታስባለህ ?
ኬፋ:__እውነት ለመናገር ዶር ደረጀ እጅግ በጣም ተወዳጅ እና ተስሚነትን በፕሮቴስታንቱ ማህበርሰብ እንዲሁም በሌሎች ዘንድ አትርፎአል ብዙ ጊዜም ወደ ሚዲያ ወቶ እንዲመክርንና እንዲያስተምረን እንፈልግ ነበር ነገር ግን እንዲ አለጠበቅነዉም ፓስተሮችንና ዘማሪያንን መስደብም አልነበረበትም ችግር ካለም በአብያተ ክርስትያናት በኩል ማስተላለፍ ይችል ነበር ነገር ግን ለሱ አይንት ሰዉ በማይሆን ሚዲያና የህዝብን ሃሳብ እኩል በማያይ ሚዲያ ላይ በመቅረቡ እጅግ አዝነናል ሁሉንም ብሄር በአንድ አይንም ማየት ነበረበት።
የሮ: አንተ ለዶር ደርጀ በሰጠኸው ምላሽ ከኦሮሚያ ዉጪም ያሉም ወጣቶች ችግር እንዳለባቸዉ ተናግረሀል ነገር ግን ደረጀ ያለዉ የኦሮሞ ወጣቶች የተለያዩ የንግድ ማእከላትን ማቃጠላችዉን እና አንዳንድ ኢንቨስትመንቶች ከ ኦሮሚያ መዉጣት መጀመራቸዉነ ተናግሮ ኣክሎም ወደለላ አካባቢዎች መዘዋወር ምጀምራችዉን ተናግረዋል፡ደረጀ የኦሮሞ ወጣት ብቻ ላይ ማትኮሩ ትክክል ነው ብለህ ታስባለህ ችግሩ የሁሉም ኢትዮጽያዊ ሆኖ ሳለ
ኬፋ:___የተቃጠለውና የወደመዉ የንግድ ማእከልም ሆነ የሰዉ ነፍስ መጥፋቱ ትክክል አይደለም ይሁን እንጂ ያልፈ ነገር አንስተን ካወራን መከፋፈላችንና መጠፋፋታችን አይቀርም እንድንረዳዳም አያደርገንም ነገር ግን ደረጀ ኦሮሚያ ላይ ብቻ ማትኮሩ ትልቅ ጉዳት ነው ምክንያቱም ኦሮሚያ ዉስጥ ብቻ ኣልነበረም አማራ ክልልም ተመሳሳይ ነበር ነገር ግን የሰዉ ነፍስ ደግሞ ከየትኛዉም ንብረት ይበልጣል ስለዚህ ችግሮች ከኦሮሚያ ብቻ አይፈልቁም ከመላዉ ኢትዮጵያ ጭምር እንጂ ሆኖም እኛ የሃሳብ ተጽኖ ማምጣት ምንችል ሰዎች ስለጥፋቱ ከማውራት ይልቅ ተስፋ ላይ ማትኮር መቻል አልብን
የሮ _ ዶር ደረጀ ለርእዮት በሚዲያ በሰጠዉ መልስ የኦሮሞ ሰላማዊ ወጣቶች በኣደባባይ ወተዉ አመጸኛዉን ቡድን ማዉገዝ አለበት ብለዋል አንተ በዚ ትስማማለህ?
ኬፋ __እኔ እንድማምነዉ የማንም ሰዉ ህይወትም ሆነ ንብረት መጥፋት የለበትም ስለዚህ ወጣቶች ሲታገሉ በአካባቢያችዉ ላሉት ሰዎችና ንብረት በብሔር ሳይለዩ መጥበቅ አለባችዉ ትግላችዉም የብሔርና የሃማኖት እኩልነት እንዲሰፍን ማረጋገጥ ነዉ ስለሆነም በብልጠትና በፍቅር ማሸነፈ አልባቸዉ
የሮ ዶር ደረጀ ሚዛናዊ አደለም ብለሃል ለዚ ማሳያዉ ደግሞ ብሆር ተኮር ግድያ በለሎችም የኢትዮጽያ ከተሞች ላይ ይፈጸማል ይህ የሚያሳየዉ ደግሞ መሰረታዊ ችግር በኢትዮጽያ ውስጥ እንዳለ ነው። ደረጀ ለርእዮት ሚዲያ እንደተናገረው በመለስ ዜናዊ ጊዜ እንደነበረዉ የብሕር ፈደራሊዝምና የብሀር ክፍፍል ከ1991 ጀምሮ በኢትዮጽያ ዉስጥ ተስፋፍቶ ነበር። ደረጀ የብሔር ፈድራሊዝምን እንደ አንድ ችግር አንስቷል ላንተም እንደዛዉ ነዉ ወይስ አሁን ያልዉ ስርኣት ጥሩ ?
ኬፋ _ እኔ እንደማስበዉ ችግሩ ብሔርን ትኩረት ያደረገ የፌደራሊዝም ስርአት ነዉ ብዬ አላምንም ምክንያቱም ይሄን ማንነትና ቋንቋ የሰጠው ፈጣሪ ነዉ ስለዚህ ማንም ሰዉ እግዚያብሄር በሰጠዉ ማንነትና ቋንቋና ባህል እንዲጠቀም ይፈቅዳል ስለዚህ በቋንቋና በባህል መለያየታችን ዉብት ነው እንጂ ምንጠፋፋበት ሊሆን አይገባም። የኔ አመለካከት የተገነባዉ እንደ አንድ መንፈሳዊ ሰዉ በመጽሀፍ ቅዱስ ነዉ መጽሃፉም እንደሚለው ሰው በሰጣን ተታሎ ከ እግዚያብሔር ሀሳብ ስለጎደለ በክርስቶስ አኢየሱስ በኩል በምታረቅ አመለካከቱን ካልቀየረ ወንድሙን መዉደድ አይችልም እደዚሁም ደግሞ ለሰዉ ሁሉ ከተሰጠዉም ትዛዝ ዋነኛዉ ወንድምህን እንድራስህ ዉደድ የሚል ነዉ ስለዝህ ሁሉም የአዳም ዘር እንደምሆኑ በ መደማመጥ በመነጋገርና በመቻቻል ወደፊት ልኔድ ያስፈልገናል
የሮ _ ከሁለት አመት ወዲ አንዳንድ ምሁራን እንደሚሉት ዲሞክራሲያዊ ሽግግሩን አላሳኩም፡ ነገር ግን እስካሁን እንድትደግፈዉ ያደረገክ ምንድነዉ?
ኬፋ _ እኔ ያለምክንያት መንግስትን መደገፍም መቃወምም አልችልም ጥሩ ነገር ሰርቶ ከሆነ ደግፋለሁ ስለዚህ ብሔር ላይና በሰዉ ነብስ ላይ ችግር ሚፈጥር ከሆነ አልደግፍም
የሮ _ ዶር ገመቺስ ቡባ የኢቫንጀሊካል መሪና የእል ቲቪ መስራች ናችዉ ባንድ ወቅት በሚኒሶታ የኦሮሞ ምሁራን በትሰበሰቡበት የነበረዉን መንግስት ነቅፎ ነበር አክሎም የኦሮሞ ፖለቲካ መሪዎች አንድ መሆን ካልቻሉና ወጣቱን መከፋፈል ከጀምሩ መችም ኦሮሚያ ዉስጥ ሰላም አይኖርም ብለዋል፡ እንደ ዶር ገምቺስና ዶር ደርጀ ፖለቲካ ዉስጥ ያሉ ሰዎችንና ስርአቱን መኮነናቸዉ ትክክል አየደለም ብለህ ታስባልህ?
ኬፋ ___እኔ ዶር ገምቺስ የተናገሩትን አልሰማዉም የደረጀን ብቻ ነዉ የሰማዉት ይሁን እንጂ ያለመረጃ መንግስትን መኮነንና ያለምክንያት መደገፍ አለበት ብዬ አላምንም ስልዚሕ ደረጀም ሆነ ገምቺስ ብሔርንና ብሔርን የሚያስታርቅ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች እንዲሰማሙ እንዲከባበሩ የሚያደርግ ሃሳብ ማመንጨት አለባችዉ ብዬ አስባለው
የሮ _ በኦሮሚያ ዉስጥ በወለጋ በታጠቁ በኦነግ እና በ ኦሮሚያ መንግስት መካከል ስላለዉ ግጭት መፍትሐው ምንድነው ብልህ ታስባልህ ?
ኬፋ_ __እኔ ፓስተር ነኝ ከ መንግስትም ሆነ ከኦነግ ሽኔ ጎን መቆም አልችልም እኔ መቆም ምችለው ከ እዉነት ጋር ብቻ ነዉ እናም ምንም አይነት ጉዳት ማንም ላይ እንዲደርስ አልፈልግም ስለዚህ መንግስትም ሆነ ኦንግ ሻኔ ወደ ዉይይት መድረክ በመቅረብ አለባችዉ። ማንም መሞት የለበትም ምክንያቱም ሰው ክቡርና በእግዚያብሔር ኣምሳለ የተፈጠረ ስልሆነ
የሮ ዶር ደረጀን ብዙ ሰዎች ለረጅም አመታት ሲገደሉ በባልፈዉ መንግስት የስልጣን ዘመን ዉስጥ የት ነበርክ ብለኸዋል፡ ነገር ግን ወደፊት አንተን ተመሳሳይ ጥያቀ ብትጠየቅስ ምንድነው መልስህ ምክንያቱም አሁን ያለውን የአብይ መንግስት ሙሉ በሙሉ ስለምትደግፍ
ኬፋ___ እኔ እግዚያብሔር ሚጠላዉን ምጠላዉ ሚወደዉን ነዉ ምወደዉ ስለዚህ እኔ ከ እግዚያብሔር ጋር ነዉ ምቆመዉ
የሮ ስለ ጃዋር ምን ታስባለህ ጥፋተኝ ነዉ ወይስ ንጹ ሰዉ ነዉ?
ኬፋ___ ይሔ ጥያቄ እኔን አይመለከተኝም እኔ ፈራጅም እግዚያብሔርም አደለዉም ያለምንም ጥፋት ታስሮ ከሆነም ፈራጅ አምላክ አለ ጥፋትም ኖሮብት ከሆነ በሀገሪቷ ህገመንግስት መሰረት በታማኝነት ብይን እንዲሰጠው እመኛለዉ እጸልይለታለውም
የሮ ለ ክርስትያን ወዳጆችህ በኦሮሚያ ውስጥ የ ኦነግን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለሚድግፉ ማስትላለፍ ምትፈልገው መልክት ካለ
ኬፋ_ እኔ የምለው ለኦነግም ሆን ለ መንግስት አካላት ማስተላለፍ ምፈልገዉ ወደ ህዝቡ ጥይት አትተኩሱ ነው ምለዉ ምክንያቱም የሚሞተዉና የሚጎዳዉ የናንተዉ አካል ነዉ ስለዚህ ህዝባቹን አትግደሉ እኔ እንደ እግዚያብሔር ሰዉ የማንንም ሰው ሞት እቃወማለዉ ስለዚህ ለኦነግ ደጋፊዎችም ለመንግስትም ማለት ምፈልገዉ ነገር ንግግርና መስማማት ብቸኛው ችግሮችን መፍቻ መንገድ መሆን አለበት።